የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ውጤታማ ሆኖ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በሰጡት መግለጫ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ድምፃቸውን መስጠታቸውን ገልጸዋል። እስከ እኩለ ሌሊት የቀጠለው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የድምፅ ቆጠራ ሂደቱ ታዛቢዎችና የፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት እየተከናወነ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የድምፅ ቆጠራው ተጠናቆ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን አመላክተዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

See less

Similar Posts