ኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ ተዘጋጅታልች

በኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፓርክነት በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ።

ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት ያልተነካ ሀብት በጂኦ-ቱሪዝም ተመራጭ ሀገር የሚያድርጋት ነው። ከዚህ አንጻር ለዩኔስኮ በወደፊቱ ሊቀርቡ የሚችሉ በርካታ የሀገሪቱ እጩ የጂኦ-ቅርስ ቦታዎች ተለይተዋል።

ከነዚህም ውስጥ በባሌ ወረዳ የሚገኘው ሶፍ-ዑመር ዋሻ፣ በቡታጅራ-ስልጤ የሚገኙት አፈጣጠሮች፣ የሰሜንና የገራልታ ተራሮች፣ የደናክል ስምጥ ሸለቆ፣ ኤርታ አሌና ወንጪ ሀይቅ እና አካባቢው ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ ውስጥ መጓዝ የምድር ጂዮሎጂያዊ ታሪክ ለማወቅ ውሳኝ ስልመሆኑ በዘርፉ ባልሙያዎቸ የሚነሳ ሲሆን “ከዓፋር ደናክል እስከ ትግራይ ገራልታ ተራሮች ድረስ በሚደረግ ጉብኝት ሁሉንም ዋና ዋና የአለት አይነቶችን ማየት ይቻላል። ይህ ሁኔታ ብዙም ሳይንገላቱ በትንሽ የርቀት ጠቃሚ ምርምር ማካሄድ ለሚፍልጉ ተመራማሪዎች መቹ አወድ የሚፈጥር ነው።

ለጂኦ-ፓርክ እጩነት ዩኔስኮ የሚፈልጋቸውን መስፈርቶች ዘላቂ አስተዳደር፣ ሳይንሳዊ ዋጋና የቱሪዝም መሠረተ ልማት ይገኙበታል። የቱሪዝም ሚኒስቴር የጂኦ-ፓርክ ምዝገባ ሥራን ለማሻሻልና ጂዮ-ቱሪዝምን በኢትዮጵያ ቱሪዝም ዘርፍ ለማስተዋወቅ እየሰራ ሲሆን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጂኦ-ቅርስ ቦታዎችዋን ለዩኔስኮ በእጩነት በማቅረብ በዓለም ጂኦ-ቱሪዝም ዘርፍ ቁልፍ ተሳታፊ ሀገር እንድትሆን እየተሰራ ይገኛል ።

Similar Posts