የመደመር እሳቤ ከሥልጣኔ አድማስ እስከ ኢኮኖሚያዊ ፍትሐዊነት፣
የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የመደመር እሳቤ (Synergy) በሕንድ የታወቀ መሆኑን መግለጻቸው፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፍልስፍና አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን የሚያሳይ ሲሆን ይህ እሳቤ ከጥንታዊ ሥልጣኔ ዕሴቶች ተነስቶ እስከ ዘመናዊ የኢኮኖሚ አስተዳደር ድረስ ያለውን ጉዞ መተንተን ይቻላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ለእያንዳንዱ ሀገር ዕድገት እርስ በእርስ መተማመንና በጋራ ጥረት በአብሮነት መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ሐሳብ የመደመር መንግሥት ካስቀመጠው ተቋማዊ ትብብር ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው::
የመደመር መንግሥት የተበታተኑ ተቋማትን በማጣመር የሥራ ቅንጅትን ማሳደግ ላይ በማተኮር ለተግባራዊ ስኬት በቅቷል።
በተለይ በግብርና ዘርፍ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የልማት ባንክና የክልል አስተዳደሮች በመናበባቸው በስንዴ ምርትና በአረንጓዴ ዐሻራ ላይ ለተገኘው እመርታ መሠረት ሆኗል።
ልማት በተናጠል ሳይሆን በብሔራዊ ራዕይ እንዲመራ ማድረግ የ”ሲነርጂ” ፍልስፍና ዋና ግብ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የኢትዮጵያ እውነተኛ ችሎታ በጥንታዊ ጥበብና በዘመናዊነት ሕልም መካከል ሚዛን መጠበቅ መሆኑን የጠቀሱት ከድንጋይ የተቀረጹት የላሊበላና የሕንድ ቤተ መቅደሶች፣የታጅመሐልና የነጃሺ ታሪካዊ ስፍራዎች፣የሁለቱ ሀገራት ጥልቅ ትሥሥር ማሳያዎች ሲሆኑ ይህ የታሪካ አንጓ ዛሬ ኢትዮጵያና ሕንድ ወደ መፃኢ ጊዜ በራስ መተማመን እንዲጓዙ ጉልበት ሆኗቸዋል።
በጥንታዊ ዕሴቶች ላይ የቆሙ ተቋማት በግልጽነትና በብቃት እንዲሠሩ በማድረግ የኢኮኖሚ መሠረትን ማጠናከር የመደመር መንግሥት ቁልፍ ምሰሶ ነው።
ሁለቱም ሀገራት በብሔራዊ መዝሙሮቻቸው ሀገራቸውን ‘እናት’ ብለው መጥራታቸው ለዜጎች እኩልነትና ለንብረት ዋስትና ያላቸውን ክብር ያሳያል። ከዚህ አንጻር ሁሉን አቀፍ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ፍሬዎች በሁሉም ክልሎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ በፍትሐዊነት እንዲዳረሱ ማድረግ የመደመር መንግሥት መርህ ነው።
ዜጎች በሕግ አግባብ የያዙትን ንብረት ዋስትና ለማረጋገጥና የኢንቨስትመንት ሕጎችን ግልጽ ለማድረግ በንብረት ፍትሐዊነት ላይ እየሠራ ይገኛል።
የመደመር መንግሥት ሕገወጥ የኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት የቴክኖሎጂ ሥርዓትን እንደ ዋና መሣሪያ በመጠቀም ፣የሰው ንክኪን ለመቀነስ በጉምሩክ፣ በግብር አሰባሰብና በፋይናንስ ሥርዓቱ (Fintech) ላይ የሚደረግ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሙስናን ለመቀነስ ዓይነተኛ ሚና እንደለው በመገንዘብ ዘርፉን ትርንስፎርም ለማደረግ ተግባራዊ ሥራዎች ጀምሯል።
በከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ የሚወሰዱ የሕግ እርምጃዎች የዜጎችን ዕምነት ለመገንባትና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶች አካል ናቸው።
በጥቅሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “መደመር” (Synergy) በሕንድ የታወቀ ነው ማለታቸው፣ ኢትዮጵያ የምትከተለው የልማትና የፖለቲካ ፍልስፍና ከዓለም አቀፍ ሳይንሳዊና ስልጣኔያዊ እውነታዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
በግብርናው ዘርፍ የታየውን ተቋማዊ ቅንጅት እና ስኬት፣ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚና ወደ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ በተመሳሳይ ጥንካሬ መሸጋገር እንዳለበት የሞዲ ንግግር እንደ ማሳሰቢያና እንደ ማበረታቻ ሊወሰድ ይገባል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication





