ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን

ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው ራዕይ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ስለመሆኑ የተመዘገቡ ውጤቶች ማሳያ ናቸው::

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ

ጥር 4/20 18 ዓ.ም

የኢትዮጵያን በ2023 አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የተያዘዉን ግብ የሚያሳካ ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆናችንን ያረጋገጠ ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ አስታወቁ፡፡

እንደ ሀገር ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲሁም አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያረጋግጥ የብዝሃ ዘርፍ የልማት ስትራቴጂ በመከተል እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ዉጤታማ መሆናቸዉ ገልጸዋል ።

የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናት አለም መለሰ ለተለያዩ የሚድያ አካላት የተከናወኑ ዋና ዋና መንግሥታዊ ሥራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም በቢሾፍቱ አቡሴራ የግንባታ ሥራው የጀመረው የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ እና ሌሎች ሀገራዊ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያ ማንሰራራት ዘመን ማሳያዎች እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚን ለመገንባት ኢትዮጵያ በጀመረችው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት በአህጉራችን ከቀዳሚዎቹ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት ተርታ መሰለፉን አንስተዋል፡፡

መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ተግባራዊ ካደረገባቸው ጊዜያት አንስቶ የኢኮኖሚ ማነቆዎችን በየጊዜው እየፈታ እንደሚገኝ እና ይህም የምርት አቅርቦትን፣ የመንግሥት ገቢን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችትን እና የወጪ ንግድን ማሳደግ መቻሉን ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር ፣ግብርናን ማዘመንና በማሻሻል፣ የአምራች ኢንዱስትሪውን ለፈጠራና ለፍጥነት ዕድገት ምቹ የሆነ ማዕቀፍ መፍጠር ፣በማዕድን ዘርፍ ሀብቶቻችንን ማወቅ፣ መግለጥና ለኢትየጵያ ብልፅግና ማዋል እንዲሁም በቱሪዝም ነባር ሀብቶቻችንን “ማስተካከል፣ ማስፋትና ማበርከት” በሚለው መርህ በመመራት የዛሬን ብቻ ሳይሆን የነገን የትውልድ ቀጣይነት እየተገነባባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ኢኮኖሚና የከተማ ልማት ሥራዎችም አስደናቂ ውጤት የተመዘገበባቸው የኢትዮጵያን ተስፋ እና አቅም ያሳዩ መሆኑን ሚኒስትሯ በመግለጫቸው አንስተዋል፡:

የያዝነው ዓመት ኢትዮጵያ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች፡ ጠንካራ ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚረዳ ሀገራዊ ምክክር እና የ7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂድበት መሆኑም በመግለጫው ተካቷል፡፡
የመደመር መንግሥት ሀገራዊ ምክክሩ አካታች እና ውጤታማ ምርጫውም ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ገለልተኛ እና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጫው በአጽንኦት ገልጾአል፡፡

በመጨረሻም፣ የተመዘገቡት ውጤቶች የመደመር መንግሥት ሕዝብ የተሳተፉበት አካታች የልማት እሳቤን በመከተል ፈጣን ሀገራዊ እድገትን ፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ የኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ልዕልናን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ በሁሉም ዘርፎች እየሰጠ የመጣው ወሳኝ አመራር ውጤት መሆኑንም መግለጫው አመላክቷል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts