ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፣ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን የአፈፃፀም ሪፖርቱን ዛሬ ጠዋት ላይ አቅርቧል።

‎ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን ዐበይት ተግባራት፣ የገጠሙትን ተግዳሮቶች እና ለተግዳሮቶቹ የሰጣቸውን መፍትሔዎች ያቀረበ ሲሆን ወደፊትም የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን በታሰበው ልክ ለማስኬድ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቁ ሚናዎችን አስቀምጧል።‎

‎በእስካሁን ስራ ከቀረቡት ቁልፍ ስኬቶች መካከል፣

‎- አካታች እና አሳታፊ የሆነ የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ

‎- የሀገራችንን 93 በመቶ የሸፈነ በ1234 ወረዳዎች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ልየታ ማድረግ ይገኙበታል።‎

‎በሌላ በኩል ኮሚሽኑ 22 ዙር የሚሆን ከተለያዩ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመመካከር የተደረገበት ሰፊ ጥረት ቢኖርም ባለው ምቹ ያልሆነ ሁኔታ በትግራይ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ ምክክር ለማድረግ አለመቻሉን አመልክቷል። ለዚህ ተግዳሮት ምላሽ ለመስጠትም ኮሚሽኑ ከመላው የትግራይ ክልል የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን እና በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ የትግራይ ክልል ተወላጆችን በማካተት በአዲስ አበባ ከተማ በማሰባሰብ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ልየታ ማካሄዱን ገልጿል።‎

‎በቀጣዩ የሀገራዊ የምክክር ምዕራፍ ኮሚሽኑ የሚከተሉትን ተግባራት ለማካሄድ አስቀምጧል:-

‎- የፖለቲካ ተዋንያንን ተሳትፎ ማጠናከር

‎- ⁠የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን መቅረፅ

‎- ⁠የሀገራዊ ምክክር ጉባኤን ማካሄድ

‎- ⁠በሀገር ደረጃ ስምምነት የተደረሰባቸውን ውጤቶች እና ምክረ ሀሳቦች ተፈፃሚነት ማመቻቸት የሚሉት የኮሚሽኑ ቀጣይ ስራዎች ውስጥ ይገኙበታል።

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

See less

Similar Posts