የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት
የተቋማት ግንባታ እና ዝግጁነትን ማረጋገጥ የመንግሥት ዐበይት ኃላፊነቶች ናቸው።
በዚህ የተነሳ ነው የሀገራችንን የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ዘርፍ ለማጠናከር የታሰበባቸው ሰፋፊ እርምጃዎችን የወሰድነው።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተደረገው የሀገራችንን ቁልፍ የመንግሥት ፋይናንስ እና ሌሎች የፋይናንስ ዘርፍ ተቋማትን ያሰባሰበው የኢትዮጵያ “የፋይናንስ እመርታ” ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ያለውን የኢኮኖሚ ሪፎርም ጉዞ መለስ ብሎ ለመገምገም እና የመጪውን ጊዜ የቅድሚያ ምልከታ ለማስቀመጥ የረዳ ጠቃሚ መድረክ ነበር።
በፊስካል አስተዳደር፣ በሞኒተሪ እና ፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም በገቢ አስተዳደር፣ በካፒታል ገበያ አስተዳደር፣ በኢንቨስትመንት አስተዳደር እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ሪፎርም ያሳካናቸውን ድሎች ለማጤን ያገዘ እና የሪፎርሞቹን ጉዞ ፍጥነት አጥብቆ በመያዝ የመራመድን እና ሰፊውን የኢኮኖሚ ሽግግር አጀንዳ የማላቅን አስፈላጊነት ለመገንዘብ የረዳ መድረክ ነበር።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication


