ሃገራዊ ለውጡ ለኢኮኖሚው ስርዓት ካስተዋወቃቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አንዱ ነው።

ሃገራዊ ለውጡ ለኢኮኖሚው ስርዓት ካስተዋወቃቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን አንዱ ነው። ‎ይህ ባለስልጣን የካፒታል ገበያ ስርዓትን ፈጠራን በማበረታታት በካፒታል ፈላጊዎች እና ካፒታል አቅራቢዎች መካከል ድልድይ የሚሆን ስርዓት እየገነባ ነው።‎

‎በኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም በሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀው የካፒታል ገበያ ስርዓት ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ሂደቶችን አልፎ ሶስት ቁልፍ ተቋማትን መፍጠር ተችሏል። እነዚህም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ እና የማዕከላዊ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ግምጃ ቤት ናቸው። እነዚህ ተቋማት ከማቋቋም ባለፈ የካፒታል ገበያ አገልግሎት የሚሰጡ 15 ተቋማት ፈቃድ አግኝተው ወደ ስራ ገብተዋል። ተቋማቱም የተከፈለ ካፒታላቸው 1.5 ቢሊየን ብር ደርሷል። በተጨማሪም 10 ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለንዋይ ገበያ ላይ ለመመዝገብ ሂደት ላይ ናቸው። በባንኮች መካከል በገበያ ላይ የተመሰረተ የገንዘብ ልውውጥ እያደገ መጥቷል። በቀጣይ ዘርፉ ኢኖቬሽን እና ስራ ፈጠራን በመደገፍ ለሃገራዊ እድገቱ የበኩሉን እንዲወጣ ለማድረግ የተጀመሩ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

‎- ሃና ተኹልቁ

‎የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

Similar Posts