የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችል ተቋማዊ አሰራርን መከተል ወሳኝ ነው።
የቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችል ተቋማዊ አሰራርን መከተል ወሳኝ ነው። ለዚህም በዘርፉ የሚሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር አስፈላጊ ነው። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዘርፉ በራሱ እድገት እንዲያስመዘግብ ከማድረግ ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች እድገት አስቻይ በመሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
አሁን ላይ በዘርፉ የተደረጉ ማሻሻያዎች አዳዲስ ኦፕሬተሮችን ወደ ስራ ከማስገባት ጀምሮ የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል። ይህ ዘርፍ በራሱ ከሚያስመዘግበው ውጤት ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች አስቻይ በመሆኑ በዘርፉ ላይ የሚሰራው ስራ ወሳኝ ነው። በተለይ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለፋይናንስ ተደራሽነት፣ ቅልጥፍና እና ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጠው ያለው አገልግሎት ተጠቃሽ ነው።
– ባልቻ ሬባ (ኢንጅነር)
የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

