ክህሎት እና አዳዲስ ስራ ፈጠራዎች (Startups)

የኢትዮጵያ መንግሥት ወጣቶች የራሳቸውን የፈጠራ ስራዎች (startups) እንዲጀምሩ፣ ወደ ስራው ዓለም እንዲቀላቀሉ እና በዘመናዊው ኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችሏቸውን ተግባራዊ ክህሎቶች ለማስጨበጥ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና መርሃ ግብሮች ላይ ሐብት ፈሰሰ እያደረገ ይገኛል። በሙያ፣ በቴክኖሎጂ እና በስራ ፈጠራ ዘርፎች ላይ ቀጥተኛ ልምድ በመስጠት፣ እነዚህ መርሃ ግብሮች አዳዲስ ፈጠራዎችን ያነቃቃሉ፤ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ፤ እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገትን በመሠረታዊነት ያፋጥናሉ። ወጣቶችን ከገበያው ፍላጎት ጋር የተጣጣሙ ክህሎቶችን ማስታጠቅ፣ የግለሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ከማሻሻሉም ባሻገር የተነቃቃ እና ለስራ ፈጣራ አመች የሆነ ኢኮኖሚ እንዲገነባ በማድረግ የልማቱ ተጠቃሚነት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲዳረስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

#PMOEthiopia

#VisionOfProsperity

#የኢትዮጵያብልጽግናራእይ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፡-

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts