በፈጣን አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ለሕዝብ አገልግሎት እንካችሁ ብለናል!

‎ለዜጎቻችን ጤና እና ለከተማችን ዕድገት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠው ይህ ስራ፤ ከፕሮጀክት የተሻገረ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ ነው! ለሁሉም ዜጋ የተገነባው ይህ ማዕከል የሚከተሉትን አካቷል፦

‎• 5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፤

‎• የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃት በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አትሌቶቻችን የክብር ሐውልቶች፤

‎• ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች፤ የኦሎምፒክ ደረጃን የሚያሟሉ የመዋኛ ገንዳ፣ የ800 ሜትር የሩጫ ትራክ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች፣ የልጆች መጫወቻዎች እና አሸዋ የተዘረጋበት ስፍራ፤

• ለማህበረሰቡ፦ ለነጋዴዎች የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆች እና 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ ተካተውበታል።

‎የተሻለች ኢትዮጵያን ማለም ብቻ ሳይሆን እኛ በተግባር እንገነባታለን!

#EthiopiaDelivers

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts