የመረጃ ሉዓላዊነት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት

”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝቼ የተመለከትኩት የዘርፉ እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ አግኝቼዋለሁ።‎

‎መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው። የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነው።‎

‎ከሁሉም በላይ፤ የመረጃ አሰባሰብና ትንተና ሥራ በሀገር ልጆች እውቀትና ክህሎት ሲከወን ማየት ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው። ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ትኩረታችን በቁጥር በሚገለጹ ውጤቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ሰው ተኮር በሆኑና በዜጎች ሕይወት በሚታዩ ተጨባጭ ለውጦችም ላይ መሆን አለበት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

Similar Posts