የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ዛሬ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙትን የቶዮ ሶላር ኢነርጅ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ኦርጅን እና ሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካን መርቀን ከፍተናል።

‎የሶላር መሠረተ ልማቶቹ በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋዋት ንጹህ ኃይል የሚያመነጩ ሲሆን፤ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7ቶን ሃይድሮጅን ያቀርባል። እነዚህ አራት ፕሮጀክቶች ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የብዙዎችን ኑሮ መደገፍ ችለዋል።

‎ ከፍተኛ የማምረት ዐቅም ያላቸው ፋብሪካዎቹ የኢትዮጵያም እምቅ ሐብት ወደ ጥቅም የቀየሩም ሆነዋል።”

#EthiopiaDelivers

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts