የመሶብ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎት

ዛሬ ስራ የጀመረው፣ አስፈላጊ የሆኑ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ የተወሰደ ትልቅ እርምጃ ነው። ለአገልግሎት የተደራጀው አውቶቡስ ሙሉ ቁሳቁስ የተሟላለትና ራሱን የቻለ የአገልግሎት ማዕከል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አሰራርን ለማረጋገጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ስርዓቶችን አቀናጅቶ የያዘ ነው።

‎አውቶቡሱ የአገልግሎት ፍሰቱን የሚያደራጅ የሰልፍ ማስተናገጃ ስርዓት ያለው ሲሆን፣ የተለያዩ የክፍያ አማራጮችንም አካቷል። ለአገልግሎቱ የሚያስፈልገውን ኃይል በከፊል ከ8 ኪሎ ዋት የፀሐይ ብርሃን የሚያገኝ ሲሆን፤ አስተማማኝ ኢንተርኔትም ተገጥሞለታል።

‎ በተጨማሪም የአገልግሎት አሰጣጡን ደህንነትና ግልፅነትን ለመከታተል ካሜራዎች ተገጥመውለታል። መፍትሔ አምጪ ሆኖ የተዘጋጀው የፈጠራ ውጤትና ተንቀሳቃሽ ክፍል፤ ከስምንት የተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ የሚከተሉትን ወሳኝ አገልግሎቶች ይሰጣል፦

‎• አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መስጠት
‎• የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ማደስ
‎• ለመንጃ ፈቃድ የሚያስፈልግ የህክምና ምርመራ ማድረግ
‎• የነዋሪነት መታወቂያ ማደስና የልደት ምዝገባ
‎• የመንጃ ፈቃድ መስጠትና የተሽከርካሪ ታርጋ ማደስ
‎• የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የመንገድ ፈንድ ክፍያን ማከናወን
‎• የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባና የመረጃ እርማት
‎• በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የሚሰጥ የቅድመ ክፍያ የኤሌክትሪክ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

‎በአጠቃላይ ይህ ተንቀሳቃሽ አውቶቡስ የስምንት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ላይ በማቀናጀት፣ ዜጎች ረጅም ርቀት ሳይጓዙ ወይም የተለያዩ ቢሮዎችን ማንኳኳት ሳያስፈልጋቸው ምቹ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ መፍትሄ ይሰጣል።

PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts