የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ!
በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው።
በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው። “
የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው!
ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ:
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication



