Similar Posts
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“ዛሬ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል። ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋት እና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።” ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 69
ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች።
ይህ ጉዞ በተቀናጀ አሰራር ተመስርቶ፣ ከመቀነስ እስከ መቋቋም ድረስ የሚያካትት የልማት እርምጃዎችን በአስተማማኝ መንገድ አቀናጅቷል። የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር፣ የደን ጭፍጨፋን በመከላከል እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። በተመሳሳይ ጊዜ የውሃ አስተዳደርን ማዘመን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተስማማ ግብርናን በመተግበር በምግብ ዋስትና…
“እውቀትን በቀላሉና በዝቅተኛ ወጪ ምናገኝበት ብቸኛ መንገድ አስተማማኝ የሆነ መሰረተ ልማት ሲኖር ብቻ ነው።” -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#PMOEthiopia ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 47
የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት።
በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን በመከተል ላይ ይገኛል። ይህም ትስስርን ማሻሻል፣ ምቹ የኑሮ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በገጠር ማሕበረሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋፋት ነው። የዚህ ዐበይት ግብ የተበታተነና የተቆራረጠ ሐብትን በማስተካከል አምራች፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ ዘላቂ ልማት ያላቸው እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ማራኪ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን መገንባት ነው። #PMOEthiopia#EthiopiaDelivers Post Views: 33
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎዴ ጉብኝት
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication See less Post Views: 38
በሚዲያና ኮሙኒኬሸን ዘርፍ ተዋናዮች መካከል ያለው ቅንጅት እየተሻሻለ መምጣቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ።
በርካታ ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በባለፉት ስድስት ወራት ውጤታማ ሥራዎችን ለመስራት መቻሉንም አንስተዋል። ይህንን ለማሳካት ለደከሙ የዘርፉ ተዋንያን በሙሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የፌዴራልና የክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የግማሽ አመት የጋራ ጉባኤ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል። በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በሰላም አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተሰራው…













