“እናልማለን፤ እንተጋለን፤ እንፈጽማለን ።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ እየሠራች ነው! ነገ የሚወሰነው ዛሬ በምንሠራው ሥራ ነው! የነገ ስኬታችን የሚቀረጸው በዛሬው ጥረታችን ነው። ከትናንት መልካም ልምዶችን በመቅሰም፣ ዛሬን በትክክል አጢኖ የነገን ራዕይ ዛሬ ላይ ሆኖ መገንባት የመንግሥታችን ጽኑ እምነትና መለያ ባህሪ ነው። ሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ ነገን ለመዋጀት መዘጋጀት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት እንደኾነ መንግሥት በፅኑ ያምናል፡፡…
የአሥራ ሦስት ወራት ፀሐይ – በዓመት 13.3 ጊጋ ዋት የሶላር ኃይል በአዳዲስ አምራቾች!ከዚህ ዐቅም ጀርባ ያሉ ፕሮጀክቶች በምስል ሲቃኙ። Post Views: 133
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 104
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡ በውይይቱም በተሰሩ ዋና ዋና ሥራዎች እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በዝርዝር ምክክር መደረጉን ገልፀዋል፡፡ የዜጎች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት የተረጋገጠባትና የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች የተስፋፉባትን ኢትዮጵያ ዕውን እናደርጋለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ Post Views: 320
ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ የዘመናት የፖለቲካ ቁርሾዎቿን እና አውዳሚ የደም አዙሪትን በመስበር፣ በሀገራዊ ምክክር ሂደት አዲስ የዲሞክራሲ እና የሰላም ምዕራፍ መክፈቷ በትናንትናው ዕለት በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ተበስሯል። ባለፉት 4 ዓመታት የዝግጅት ምዕራፍ ውስጥ አልፎ ከ4 ሺህ በላይ ወኪሎችን በማሳተፍ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለ46 ቀናት የተካሄደው ይህ ታሪካዊ ጉባኤ የሀገረ-መንግሥት ታሪካዊ ተቃርኖዎች በአፈሙዝ…
● ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. በተካሄደው 7ኛው አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትውልድ ስፍራቸው በሻሻ ወረዳ በመገኘት ድምጻቸውን የሰጡ ሲሆን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክትም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሀገር ፍቅር ላሳየው ቁርጠኝነትና ለከፈለው መስዋዕትነት ታላቅ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰኔ 14…