የፕሪቶሪያ ስምምነት መነሻና መድረሻው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ማክበር ነው!






ብዝኃነታችን የምንደምቅበት ጌጥ፣ የተደመረ ዐቅማችን ማሳያ ነው! ኢትዮጵያ የብዝኃ ማንነቶች ድምር ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሚኖሩበት የአየር ንብረት እስከ አመጋገባቸው፤ ከአመራረታቸው እስከ አለባበሳቸው፤ ከሃይማኖታቸው እስከ ፖለቲካዊ አመለካከታቸው በርካታ ብዝኃነቶች ያስጌጧቸዋል፡፡ የእነዚህ ብዝኃነቶች ድምር ደግሞ የኢትዮጵያ የማድረግ ዐቅም ነው፡፡ የኢትዮጵያውያን ብዝኃነት ለዘመናት የማይታረቁ የልዩነትና ግጭት ምንጭ ተደርጎ እንዲታይ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ያለመታከት ሠርተዋል፡፡ በዚህም በየዘመኑ የታዩ ስኬታማ ድሎችን በአጭር…
ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ ላይ ለመሥራት እያደረገች ያለውን ጥረት እና የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስተዋወቅ 5ኛዉን የጳጉሜን ቀን “የነገዉ ቀን” በሚል ስያሜ እና “ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ” በሚል መሪ መልእክት እያከበረች ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከራሷ ባሻገር የአፍሪካን ማንሰራራት ለማብሰር ዛሬ ላይ ነገዋን እየሠራች ነው፡፡ ለአምስተኛዉ የኢንዱስትሪ አቢዮት የሚመጥን ትውልድ መቅረጽን፣ ለኢንዱስትሪ ዕድገቱ የሚመጥን ታዳሻ ኃይል ማቅረብን፣ የዘመኑ ከተሞችን መፍጠርን፣…
መጋቢት 22 /2018 ዓ.ም የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት ስምንት ዓመታት የተከተለው ንቁና ስልታዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የሀገራችንን የውጭ ግንኙነት ለዘመናት በተዛባ መልኩ ይዞት ከነበረው “በጠላቶች የመከበብ እይታ” በማላቀቅ ለላቀ ዓለም አቀፋዊ ከፍታ የሚመጥን መሠረት ጥሏል። የለውጡ መንግሥት የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዋነኛ መለኪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ነው። ሀገራችን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የራሷን የሉዓላዊነትና የልማት ፍላጎት ማዕከል…
ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጊዜ የሌላውን ፍለጋ ጥቃትና ወረራ ፈፅማ አታውቅም፡፡ በአንፃሩ ጠላቶችዋ በተለያዩ ዘመናት በተደጋጋሚ ከሩቅና ከቅርብ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊያን ተሸንፈው እጅ የሰጡበት ወቅት የለም፡፡ ሁሉንም ወራሪዎች ድል አድርገው አንገት በማስደፋት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር አስጠብቋል፡፡ከእነዚህ የወረራ ታሪክና የድል አድራጊነታችን የሁል ጊዜ ኩራታችን የሆነው ውቅያኖስን አቋርጠው ኢትዮጵያ ላይ ወረራ በመፈፀም ሉዓላዊነታችንን…
የአማራ ክልል ሕዝብ ባለፉት ጥቂት ዓመታት መክፈል የማይገባዉን ውድ ዋጋ በጥቂት ጥቅመኞች ምክንያት እየከፈለ ይገኛል፡፡ የፋኖን ታሪካዊ አነሣሥ እና ዓላማ ባልተከተለ አግባብ ራሳቸዉን በፋኖ ስም የሚጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች በቀሰቀሱት ግጭት የአማራ ክልል ሰላም እና ልማት ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ፋኖ ሀገር በባዕድ ወራሪ እጅ በወደቀችበት እና ማእከላዊ መንግሥት በግዞት በቆየበት ወቅት ሀገርን ለማዳን የተደረገ ተጋድሎ የተመራበት ድንቅ…