ሚዲያዎች የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሁሉም ዜጎች የእለት ከእለት ልምምድ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት ቀጣይነት ያላቸው እና ለውጥ የሚያመጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ይዘቶችን መስራት ይጠበቃል።

አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በጋራ በመተባበር የሁለተኛው ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን መሰረታዊ አላማና ግቦችን፤ እንዲሁም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

አካባቢን ለመጠበቅ እና ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚዲያ ባለሞያዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑን ገልፀው ይህን ለማድረግ የሚዲያ ባለሞያዎች ስለጉዳዩ ትክክለኛው አረዳድና ጥሩ መረጃ ሊኖራቸው እንደሚገባ አመላክተዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ከሌሎች ስራዎች በተለየ የሁሉንም ዜጎች ተሳትፎ የሚጠይቅ ተግባር እንደመሆኑ የሚዲያ ባለሞያዎች ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ ከምትሰራቸው የልማት ተግባራት መካከል አንዱ የአካባቢ ጥበቃ ስራ መሆኑን ያነሱት አቶ ተስፋሁን፣ ለዚህም የሕግ ማዕቀፎች ማዘጋጀት፣ የተቋማት መጠናከር ጨምሮ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በበኩላቸው፣ በሀገራችን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ ሰፋፊ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። የኮሪደር ልማት፣ አረንጓዴ አሻራና የወንዝ ዳርቻ የልማት ስራዎች እና በ1ኛው ዙር የጽዱ ኢትዮጽያ ንቅናቄ የተተገበሩ ተግባራትን እና የተገኙ ውጤቶችን በማሳያነት አንስተዋል።

በሁለተኛው ዙር ጽዱ ኢትዮጽያ ንቅናቄ ውጤት እንዲያመጣ ቀጣይነት ያለው ህዝባዊ ግንዛቤ በመፍጠር እረገድ የሚዲያው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዚህም ባለ ስልጣኑ እና አጋር ተቋማት በቀጣይ ስድስት ወራት ለመተግበር የታቀዱ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ስራዎችን ሚዲያው የስራው አካል አድርጎ እንዲሰራ አስገዝበዋል።

አክለውም ለአካባቢ ብክለት የሚዳርጉ የፕላስቲክ ምርቶች ውጤቶች መጠቀም በአካባቢና በሰዎች ደህንነትና ጤና ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቆጣጠር አዲሱ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ በብክለት ምክንያት በአካባቢና በሰዎች ደህንነት ላይ ክልክላ በማድረግ በሥርዓተ ምህዳር ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት መከላከል እንደሚያስችል አብራርተዋል።

Similar Posts