በተባበረ ክንድ የኢትዮጵን ብልፅግና እዉን እናደርጋለን፡፡ ‘

ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸዉ ጥረቶች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ለላቀ ስኬትም ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት 2ኛዉን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡ ይህም በኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለዉን ሚና የሚጎላ፣ በሥርዐተ ምግብ ዙሪያ የጀመረቻቸዉን ስኬታማ ተግባራት የሚያበረታታ ነው፡፡ ከዐራት ዓመታት…
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና በህዝቡ ትብብር እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ በእጅጉ ሊያሳድጉ የሚችሉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ያዘጋጁት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቡድን ጉብኝት በሁለተኛ ቀን ቆይታው በድሬዳዋ እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል። በዛሬው እለት የድሬዳዋ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ የድሬዳዋ ስታዲየም ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ የድሬዳዋ…
በዚህም መሰረት: 1. የመካከለኛ ዘመን 2018-2022 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ ማዕቀፉ የመንግስትን ገቢ መሠረት በማስፋት ወጪ ለመሸፈንና የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ፣ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ማዕቀፉ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ…
ተለዋዋጭ ነባራዊ ኹኔታዎችንና ሀገራዊ አቅጣጫዎችን ታሳቢ ያደረገ የሚዲያ እና ኩሙኒኬሽን ሥራ በበጀት ዓመቱ ትኩረት እንደሚሰጠዉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ገለጹ። የአገልግሎቱ የ2018 በጀት ዓመት የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዕቅድ ላይ ውይይቶች ተደርገዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ አቅጣጫ ያስቀመጡት ዶ.ር ለገሠ ” ነባራዊ ኹኔታዎችን መሠረት አድርጎ የኢትዮጵያን ማንሠራራት ማጽናት ላይ ያተኮረ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሥራ…
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ አተኩረው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኃይል አቅርቦት እና የሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮችን በተመለከተ ለተነሡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያም በቀጣይ መስከረም ታላቁ የኅዳሴ ግድብ እንደሚመረቅ በመግለጽ በመርሐ ግብሩ ላይ ከግድቡ ተጠቃሚ የኾኑ የታችኞቹ የተፋሰስ አገራት መንግሥታት እንዲታደሙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዓባይ…