በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ላይ የተጨመረ ትልቅ እመርታ!

‎‎የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ሆስፒታሉ አዲስ አበባን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተቀመጠውን ሀገራዊ ግብ ከመደገፉም በላይ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል።

‎‎ የተቋሙ አሁናዊ አቅም እና ርዕይ:-

‎በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ግዙፉ ሆስፒታል 17 ዘመናዊ ህንጻዎችንና 500 አልጋዎችን ይዟል። ተቋሙ የተገነባው የኢትዮጵያን የህክምና አቅም ለማጠናከር፣ የላቁ የህክምና አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማስፋት እና የልዩ ህክምና መዳረሻ እንድትሆን የተጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ነው።

‎‎የላቀ የህክምና ቴክኖሎጂ:-

‎ሆስፒታሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘ የዲጂታል የቅድመ ካንሰር እና ድህረ ካንሰር የምርመራ ማሽን ጨምሮ የሚከተሉትን ዘመናዊ

‎ህክምና ቴክኖሎጂዎች አካቷል፦

‎• ባለ 3-ቴስላ ኤም.አር.አይ (3-Tesla MRI) ማሽን

‎• ባለ 640-ስላይስ ሲቲ ስካን (640-slice CT scan)

‎• በድምጽ የሚታዘዝ የካቴተራይዜሽን ላብራቶሪ (Cath Lab)

‎• የ3ዲ (3D) ማሞግራፊ መሳሪያ

‎• የሮቦቲክስ ላብራቶሪ (TLA) መሳሪያ፤

‎‎እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ ውስብስብ የሆኑ የጤና እክሎችን የመመርመር እና የማከም አቅምን በእጅጉ ያሻሽላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

‎‎#PMOEthiopia#EthiopiaDelivers

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

See less

Similar Posts