በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የሚነቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭን እየተቀበሉ ነዉ!

መንግስት በተለያዩ ሀገሪቱ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰዉ የህዝቡን ሰላም የሚያዉኩ አካላትን ለመቆጣጠር የሰላም አማራጮችን ሲከተል ቆይቷል፡፡በዚህም በርካታ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበልና የታህድሶ ስልጠና በመዉሰድ ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡ ሰሞኑን በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተሳሳተ ዓላማ ወደ ጫካ ገብተው የነበሩ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ገብተዋል።

በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለይ በአራቱም ወለጋ ዞኖች፣ በምዕራብ ሸዋ፣ እንዲሁም በመስራቅ ሸዋ ዞን አያሌ ታጣቂዎች እጅ በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ እየተቀላቀሉ ማህበራዊ ህይወታቸውን እየኖሩ ነው። በተመሳሳይ በአማራ ከልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ደቡብ ወሎ፣ እንዲሁም ምስራቅና ምስራቅ ጎጀም ዞኖች ዉስጥ በርካታ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ ተቀብሎ እየገቡ መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ከስኬታማ ህይወት ባሻገር የህዝብና ሀገርን ክብር መጠበቅ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡

ታጣቂዎቹ በተሳሳተ መረጃ የኦነግ ሸኔና የፋኖ የጽንፈኛ ቡድኖችን መቀላቀላቸውን በመግለጽ፣ በትጥቅ ትግል የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን በመረዳት የመንግስትን የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን ተናግረዋል። ለህዝብ ሰላም እና ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት የመንግስትን የሰላም አማራጭ የተቀበሉት ታጣቂዎች ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን እስካሁን 65ሺህ 500 ታጣቂዎች በተሐድሶ ሂደት አልፈው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን ገልጿል፡፡ኮሚሽኑ በሀገር ሽማግሌዎችና በሀይማኖት አባቶች የቀረቡ ጥሪዎችን ተቀብለው ወደ ሰላም የሚመጡ የቀድሞ ታጣቂዎች የሀገሪቱ የሰላምና የልማት ኃይል እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንምም አሳዉቋል፡፡

Similar Posts