በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል
በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በሳይበር ደህንነት ላይ በርካታ አስቻይ መሰረቶች ተጥለዋል። በዚህም የራሳችንን ክላውድ መሰረተ ልማት በመገንባት በኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎት መተማመን መፍጠር ተችሏል። ለጸጥታ ተቋማትም የዲጂታል ፎረንሲክ ላብ በመገንባት ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል። በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የሳይበር ደህንነት ስትራቴጂካዊ ትኩረት ተሰጥቶታል። በዚህም የማይበገር ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማት መገንባት፣ የህዝብ መሰረተ ልማትን ማዘመን፣ የአደጋ ምላሽ መስጫ ማዕከል የማቋቋምና የግል ተቋማትን ያካተተ የሳይበር ደህንነት ስራ እንዲጎለብት ይሰራል።
ትዕግስት ሀሚድ
የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር

