በፈጣን አፈጻጸም ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የአዲስ ስፖርት ፓርክን ለሕዝብ አገልግሎት እንካችሁ ብለናል!
ለዜጎቻችን ጤና እና ለከተማችን ዕድገት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠው ይህ ስራ፤ ከፕሮጀክት የተሻገረ፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ ነው! ለሁሉም ዜጋ የተገነባው ይህ ማዕከል የሚከተሉትን አካቷል፦
• 5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የስፖርት እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራ፤
• የቀጣዩን ትውልድ ለማነቃቃት በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ የ15 አትሌቶቻችን የክብር ሐውልቶች፤
• ዘመናዊ መሰረተ ልማቶች፤ የኦሎምፒክ ደረጃን የሚያሟሉ የመዋኛ ገንዳ፣ የ800 ሜትር የሩጫ ትራክ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግር ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና የሜዳ ቴኒስ ሜዳዎች፣ የልጆች መጫወቻዎች እና አሸዋ የተዘረጋበት ስፍራ፤
• ለማህበረሰቡ፦ ለነጋዴዎች የሚሆኑ 105 አዳዲስ የንግድ ሱቆች እና 3 ሺህ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሰፊ ፕላዛ ተካተውበታል።
የተሻለች ኢትዮጵያን ማለም ብቻ ሳይሆን እኛ በተግባር እንገነባታለን!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication









