በ #አረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞች በመታደስ ላይ ፤

በ #አረንጓዴዓሻራ መርሃ ግብር አማካኝነት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞች በመታደስ ላይ ሲሆኑ፤ የተተከሉ ዛፎች እና የለሙ የሕዝብ መናፈሻዎች የከተማ አካባቢዎችን በእጅጉ በማስዋብ እና በመለወጥ ላይ ናቸው።

ቀደም ሲል በኮንክሪት ግንባታዎች ተውጠው የነበሩ ስፍራዎች አሁን ወደ ምቹ የመኖሪያና ማራኪ አካባቢነት እየተቀየሩ ነው። እነዚህ አረንጓዴ ስፍራዎች አካባቢን በመጠበቅና የሥነ-ሕይወት ስብጥርን በማበልጸግ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን፣ ጤናማና ብቁ ማህበረሰብ እንዲገነባም ያግዛሉ።

መርሃ ግብሩ ለመዝናኛ፣ ለማህበራዊ ግንኙነት እና ለተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ቦታዎችን እውን በማድረግ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር ሲሆን፤ ይህም መንግሥት ለዘላቂ እና ሰው ተኮር ለሆነ የከተማ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

#PMOEthiopia

#VisionOfProsperity

#የኢትዮጵያብልጽግናራእይ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts