ኑ ታሪክ እንስራ !

በዛሬዉ እለት ኢትዮጵያዊያን ታሪክ ለመስራት ከጫፍ ጫፍ በነቂስ እየወጡ ነዉ፡፡ ከብረት በጠነከረዉ አንድነታችን ዘር ፣ ቀለም ፣ ሀይማኖት ፣ እድሜ ፣ ፆታ ሳይለየዉ ወርቃማ ታሪክ ለማስመዝገብ አንድ ብለን ጀምረናል።
በዛሬዉ እለት በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የአንድነታችን ሃይል ደምቆ ይታያል፡፡ እኛ አትዮያዊያን በአንድነት ተነስተን ፣ በህብረት ተባብረን ፣ በአንድ ጀምበር 600 ሚለዮን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፋለን። ሁሌም የሚዘከር ታሪክ ለትውልድ እናስተላልፋለን።
ኑ ታሪክ እንስራ! ኢትዮጵያን በስጦታችን እናድምቃት!
