አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ሲመሰረት፤

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ እንደ ወርቅ በእሳት ተፈትኖ ያለፈ እና በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። በዲሞክራሲያዊ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም ኢትዮጵያ ግን አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተዋል። እንደ ሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች ማሸነፍ የምንችለው እጅ ለእጅ ተያይዘን እንደ ወንድማማች ስንጓዝ እንደሆነ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዓለማችን በፍጥነትና በማይገመት ሁኔታ ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት መጪውን ዘመን በተጠንቀቅ መጠበቅ ትልቅ ምንዳ እንዳለው አስገንዝበዋል። ስለዚህም ለሀገር የሚበጀውን በጥበብ መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ታላቅ አደራ መሆኑን በንግግራቸው አስተላልፈዋል።‎

‎#MedemerGovernment

‎#PMOEthiopia

Similar Posts