ኢትዮጵያን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች ዕምርታዊ ዉጤቶችን እያስመዘገቡ ነዉ

ህዳር 5/2018 ዓ.ም

እንደ ሀገር ሁሉንም አከባቢዎች ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብርሃን ለማሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች እምርታዊ ዉጤቶችን እያስገኙ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ ይገኛል፡፡

“ዲሞክራሲያዊ አንድነት፣ ለህብረብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበረውን 20ኛዉ የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓልን በማስመለከት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የፌድሬሽን ም/ቤት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጋራ በመሆን የክልሉን ዕምቅ ሀብቶችን ለማስተዋወቅ በሆሳዕና ከተማ እየተሰሩ ያሉ ዐጠቃላይ መሰረተ ልማቶችን ተዘዋዉሮ ምልከታ አድርጓል፡፡

በምልከታዉ ላይ የፌዴሬሽን ም/ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ አገኘዉ ተሻገር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ እንዳሻዉ ጣሰዉ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ምልከታ ከተደረገባቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች፣ የቢሮ ግንባታዎች፣ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች፣ የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ሂደት፣ እንዲሁም በርካታ የልማት እንቅስቃሴዎች በዉጤት የታጀቡ መሆኑን ማየት ተችሏል፡፡

በዓሉ ለሀገር ግንባታ ሂደት ወሳኝ ሚና የሚጫወት እና ሁሉን አቀፍ የልማት ሥራዎችን ይበልጥ እንዲነቃቁ የሚያደርግ በመሆኑ ሚዲያና ኮሙኒከኬሽን የክልሉን የተፈጥሮ ጸጋዎች፣ የቱርዝም መስህቦችና መዳረሻዎችን በላቀ ሁኔታ ለማስተዋወቅ የሚጠበቅበትን አዎንታዊ ድርሻ የሚያበረክት ይሆናል፡፡

Similar Posts