ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ጀንበር #600_ሚሊየን_ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ አሻራቸዉን አሳረፉ።


ዶክተር ለገሰ ቱሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር የሲቪሽ ሰርቪስ አገልግሎቱ ከማንኛውም ኃላ ቀር አሰራርና አመለካከቶች ተላቆ ዘመኑ የሚፈልገውን ብታቅና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል በርካታ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች “አገልጋይና ስልጡን ሲቪስ ሰርቪስ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ“ በሚል ርዕስ በተካሄደ ውይይት ማጠቃለያ…
(ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም) በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተመዘገቡ በርካታ የልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድን በአዳማ ከተማ እየገመገሙ ነው። የተቋሙ የዘንድሮ አፈጻጸም ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዉጤታማ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች…
የአረንጓዴ ዐሻራ መረሃ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተያዘዉን ግብ እዉን የሚያደርግ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽ አገልግሎት ገለጸ፡፡ መረሃ ግብሩ የውሃ ሀብትንና የብዝሃ ህይወት ጥበቃን በማረጋገጥ ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የቤተ መንግሥት አስተዳደር እና የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አመራርና ሠራተኞች፣ የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት በጋራ ትናንት ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በመልካሳ ቤተመንግሥት የችግኝ…
መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዪ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት እና ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በተገባደደዉ የበጀት አመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2016 የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20,664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል። ፕሮጀክቶቹ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በሁለት ዙር የሚመረቁ ይሆናል።እነዚህ ፕሮጀክቶች በዋናነት የህብረተሰቡን የዘመናት የመልማት…
መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለጳጉሜ 5 የነገ ቀን እና ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ በሠላም አደረሳችሁ! ነገ የጊዜ መቍጠሪያ ብቻ አይደለም፤ ነገ ተስፋ፣ ምኞት፣ ስንቅ፣ ለዛሬ መነሣሣትና ትጋት ምክንያት ጭምር ነው፡፡ ነገ ሁላችንም ለማየት የምንጓጓለት፣ የተሻለ ሕይወትና ስኬት እንዲኖረን የምንመኘዉ መሻታችን ነው፡፡ እንደግለሰብ የተሻለ ነገን እንመኛለን፤ እንደቤተሰብ የተሻለና የጋራ ደስታና ተድላ ያለው ነገን እናልማለን፤ እንደሀገር ሰላም፣ ደስታ፣ ብልጽግና…
መንግስት ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣውን ሪፖርት አስመልክቶ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ ምላሹም እንደሚከተለው ይቀርባል፡- ሂዩማን ራይትስ ዎች የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ. ጁን 1 ቀን 2023 (ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም) በሀገራችን በአንዳንድ አካባቢዎች ጉልህ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚገልጽ መሰረተ ቢስ ሪፖርት አውጥቷል ብሏል። በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረው ግጭት በርካታ አካባቢዎችን ለጉዳት ያጋለጠ ቢሆንም በልዩ ሁኔታ የተወሰነ…