ኢትዮጵያ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚላመድና የማይበገር የልማት ግስጋሴዋን በተጨባጭ ውጤቶች እያስመሰከረች ቀጥላለች።

ይህ ጉዞ በተቀናጀ አሰራር ተመስርቶ፣ ከመቀነስ እስከ መቋቋም ድረስ የሚያካትት የልማት እርምጃዎችን በአስተማማኝ መንገድ አቀናጅቷል። ‎የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቀነስ የካርቦን ልቀትን መቆጣጠር፣ የደን ጭፍጨፋን በመከላከል እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገሪቱን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል። በተመሳሳይ ጊዜ የውሃ አስተዳደርን ማዘመን እና ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተስማማ ግብርናን በመተግበር በምግብ ዋስትና ላይ የሚታይ ለውጥ አመጥቷል።

‎‎በከተማ ልማት ዘርፍ የወንዝ ዳር ልማቶችን ማስፋፋት፣ አረንጓዴና ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እና ሞተር-አልባ ትራንስፖርትን ማስፋፋት ከተሞችን ከሥነ-ምህዳር ጋር የማስታረቅ አዲስ አቅጣጫ ፈጥሯል። በሀገር አቀፍ ደረጃም የከርሰ ምድር እና የገፀ ምድር ውሃን ለመስኖ ማዋል፣ ተስማሚ ዝርያዎችን መጠቀም እና የእንስሳት ሀብትን ማበረታታት፤ የሥርዓተ-ምግብ ዋስትናን እያጠናከረ ይገኛል።

‎‎በኢነርጂ ዘርፍ የአረንጓዴ ኃይል ምንጮችን ማስፋፋት ልማትን የሚያነቃቃ ትልቅ ዐቅም ሆኖ ተገንብቷል፤ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ ትራንስፖርት መሠረት እየሆነም ነው።

‎እነዚህ ሁሉ ጥረቶች:-

‎LT-LEDS: (የረጅም ጊዜ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ልማት ስትራቴጂ)፣

‎TYDP: (የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ)፣

‎NDC: (በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተገበሩ ተሳትፎዎች)፣

‎NAP: (የሀገር አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ዕቅድ) ያሉ ማዕቀፎች እና የዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በተቀናጀ መልኩ በመተግበራቸው፣ ኢትዮጵያ ለትውልድ የምታሻግረው ዘላቂ እና አረንጓዴ ነገን መሠረት እየጣለች ነው።

‎ይህ ጉዞ ምላሽ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያን ብሩህ መፃዒ ጊዜ የሚገነባ አቅጣጫ ነው::

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts