“እንደ ሃገር የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ትርጉም ባለው የኮሙኒኬሽን ስራ መደገፍ ይገባቸዋል፡፡”

ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፣ በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እንዲሁም በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች ተገኝተው የተከናወኑ የልማትና የኮሙኒኬሽን ተግባራትን ምልከታ አድርገዋል::
በጉብኝቱ ወቅት በዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት የተሰሩ ስራዎች ለሌሎች አካባቢዎች በተምሳሌትነት የሚወሰዱ መሆናቸው ገልጸው በሰላም ረገድ የተገኘው ስኬት በልማቱ መስክም ለመድገም የተሰራው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመሩና በልዩ ትኩረት ክትትል የሚደረግባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያሉ አፈጻጸሞችን ምልከታ ያደረጉባቸው ሲሆን ከተሞችን ከማዘመንና ዲጅታላይዝድ ከማድረግ አንጻር እየተሰራ ያለው የስማርት ሲቲ ልማት ስራዎችን አደራጅቶ በመያዝ የዘመነ የከተማ አስተዳደርና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን በማፋጠን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሊያስነሱ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመፍታት በሚያስችል መልክ በኮምቦልቻ እና ደሴ ከተማ አስተዳደሮች እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በኮሪደር ልማት ረገድም በሁለቱም ከተማ አስተዳድሮች ህዝቡን ባለቤት ያደረገ፣ በፍጥነትና በጥራት እየተሰራ መሆኑን ከምልከታው መረዳት ተችሏል ። የኮሪደር ልማት ከተሞችን ከማስዋብም ባሻገር ለኢንቨስትመንት፣ ለኑሮ እና ለጤናማ እድገት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡
ሌላው በጉብኝቱ ትኩረት ያደረጉበት በሰው ተኮር ተግባራት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ሲሆኑ ይህም ለአቅመ ደካሞች እና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመገንባት ላይ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እና በደሴ ከተማ ከ11ሺህ በላይ እና በኮምቦልቻ ከተማ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የምገባ መርሃ ግብር ይገኙበታዋል።
የተማሪዎች ምገባ በየቦታው በተጠናከረ ደረጃ መካሄዱ ተማሪዎች ትኩረታቸውን ትምህርት ላይ ብቻ እንዲያደርጉ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን ይህም መንግሥት በዕውቀት የተገነባ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ላይ እየሰራ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ሃገራችን ለጀመረችው የለውጥ ትልም መሰረት የሆኑትን የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ፤ ገበታ ለትውልድ፤ ገበታ ለሃገር፤እና በስፋት እየተተገበሩ ያሉ ሰው ተኮር ተግባራቶች የነገዋን ባለ ብሩህ ተስፋ ሃገር ቀድመን ዕንድናይ እድል ይሰጣል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው በክልሉ ብሎም በሃገር ደረጃ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ዘርፎች የሚከናወኑ ተግባራትን ትርጉም ባለው መልኩ ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ የኮሙኒኬሽን ዘርፉ የቅድሚያ ተግባር መሆን እንደሚገባው አጽንኦት ገልጸዋል፡፡
የሎጎ ሃይቅ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት፣ የደሴና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮች የኮሪደር ልማት፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የስንዴና የሌማት ትሩፋት የልማት ስራዎች ምልከታ ከተደረገባቸው ቦታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡