ከታሪካዊ መካኖች እስከ አስደናቂ መልክዓ ምድሮች የኢትዮጵያ ነባር እና አዳዲስ የቱሪዝም ስፍራዎች እውነተኛ መዳረሻ እየሆኑ መጥተዋል
ከታሪካዊ መካኖች እስከ አስደናቂ መልክዓ ምድሮች የኢትዮጵያ ነባር እና አዳዲስ የቱሪዝም ስፍራዎች እውነተኛ መዳረሻ እየሆኑ መጥተዋል። የተሻሉ አዳዲስ መንገዶች፣ ሆቴሎች፣ የጎብኝ አገልግሎቶች ለዚህ እድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል። እነዚህ መሻሻሎች የሀገራችንን ታሪካዊ ስፍራዎች እና አስደማሚ የተፈጥሮ መዳረሻዎች የጉብኝት ሂደቶችን ቀላል እና ምቹ አድርገዋል። ቱሪዝም ሥራ ይፈጥራል፣ የየአካባቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ያጠናክራል፣ የኢትዮጵያን የባሕል ሀብት ያስተዋውቃል። ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጎብኝዎች እና በሚጎበኟቸው መዳረሻዎች ላይ የምንሰራው ሥራ ይበልጥ የተቆራኘና የበለጸገ ነገን ለመፍጠር የምንሰራው ዘላቂ ሥራ ነው።
