የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ከተማዋን ለኗሪዎች ምቹ ከማድረጉም ጎን ለጎን የቱሪስት ፍሰት የሚጨምር ነው።

ሰላማዊት ካሳ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዴኤታ

የሀዋሳ ከተማ ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን እና የቱሪስት መዳረሻነቷን ለማስፋት ብሎም ለወጣቶች የስራ ዕድልን ለመፍጠር እየተሰሩ ከሚገኙ የልማት ስራዎች አንዱ እና ዋንኛው የኮሪደር ልማት መሆኑን አመላክተዋል።

ሚንስትር ዴታዋ ይህን ያሉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በሐዋሳ ከተማ እየተሰሩ ያሉ ልማት እና የኮሪደር ስራዎች ላይ እያደረገ በሚገኘው የሚዲያ ምልከታ ወቅት ነው።

የኮሪደር ልማት ስራው በክልሎችም ሆነ በአዲስ አበባ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን ቅንጅት ለመፍጠር አስፈላጊ መሆኑ አንስተዋል። ኢትዮጵያ የፊታችን ነሐሴ 29/2016 ዓ.ም በምታስተናግደው የአፍሪካ የከተሞች ፎረም ልምዳቸውን ከሚያካፍሉ ትላልቅ ከተሞች መካከል የሀዋሳ ከተማ አንዷ መሆኗን ጠቁመዋል።

Similar Posts