የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ተኛ የስራ ዘመን የጋራ ጉባኤ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴን የኢፌዴሪ መንግስት ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ከቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተረክበዋል።


አዲሱ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን ከቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተረክበዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይወት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር። እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት አመራሮች ጋር…
የዓለም መሪዎች በ100 ቀናት የሰሩት ስራዎች ላይ ዜናዎች እንደሚወጣ ያነሱት የመንግሥት ኮሙኒኬሺን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትአለም መለስ በአፍሪካ ግን ይህ አሰራር ያልተለመደ መሆኑን አንስተዋል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች አያልሙም ካለሙም አይተገብሩም የሚል ትቺት እንዳለም ግልፀዋል፡፡ ከለውጡ ወዲህ በኢትዮጵያ በ100 ቀናት ዉስጥ የሚነገር ታሪክ ነጥሎ ያየ፤ ሃሳቡን መሬት የሚያወርድ፤ አካሄዱን ደግሞ በትክክል ከህዝብ ተጠቃሚነት ጋር ማቆራኘት የሚችል አመራር…
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገር ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት ነው። ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው። በአዳም ምክንያት ወደ ምድር የወረደው ሰው፣ በክርስቶስ ምክንያት ወደላይ የወጣበት ነው። የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ…
ታኅሣሥ 21/2018 ዓ.ም የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መንግሥት የኢትየጰያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው በማለት ከነደፋቸው ትልሞች መሐከል ዲጂታል ኢትዮጵያን መገንባት ትልቅ ትኩረት የሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን መፃዒ እድል በዛሬና በነገ ትውልድ ፈጠራና ቴክኖሎጂ እድገት ላይ ለመገንባት ያለመው ዲጂታል ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ጥራት ያለው ከዘመኑ ጋር የሚጓዝ አካታች ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችል ውጤት እየታየበት ይገኛል፡፡ እንደሚታወቀው ይህን ትልም…
“ብዝኃነት ዐቅም፣ ውበት እና ጌጥ ነው፤ በዚያዉ ልክ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ አስገነዘቡ፡፡ “ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ” በሚል መሪ መልእክት የኅብር ቀን በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተከብሯል፡፡ በመድረኩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ብዝኃነት የተሰናሰነ ዐቅም መኾኑን በመረዳት የማንነት፣ የሐሳብ፣ የታሪክ፣ የባህል እና የመሳሰሉትን ብዝኃነቶች የሚያስተናግድ ሥርዐት እየዳበረ እንደሚገኝ…