የህዳሴ ግድብ በተርባይን ከሚያልፈው ውሃ በተጨማሪ በግድቡ ውሃ ማስተንፈሻ በሮች / Spillway/ በአንድ ሰከንድ 2800 ሜትር ኪዮብ ውሃ ወደ ተፋሰስ ሀገራት መልቀቅ ጀምራል።


(ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም) በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት እንደ ሀገር የተመዘገቡ በርካታ የልማትና ዴሞክራሲ ግንባታ ስኬቶች፣ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድን በአዳማ ከተማ እየገመገሙ ነው። የተቋሙ የዘንድሮ አፈጻጸም ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ዉጤታማ የኮሙኒኬሽን ሥራዎች…
“ዓላማ ተኮር ተግባቦት ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ መልእክት የፌዴራል ተቋማት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ውይይት ተካሂዷል፡፡ በአፍሪካ የአመራር ልሕቀት አካዳሚ ዛሬ የተካሄደዉ የውይይት መድረክ ላይ የዘርፉን አጠቃላይ አቅጣጫ ያመላከቱት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ (ዶ.ር) ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት በተመዘገቡ ኹለንተናዊ ስኬቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ጉልህ ሚና መጫወቱን አውስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ…
መንግስት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዪ መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት እና ተደራሽ የማድረግ ስራዎችን በተገባደደዉ የበጀት አመት ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል።በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በ2016 የበጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 20,664 ፕሮጀክቶች ለምረቃ ተዘጋጅተዋል። ፕሮጀክቶቹ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ በሁለት ዙር የሚመረቁ ይሆናል።እነዚህ ፕሮጀክቶች በዋናነት የህብረተሰቡን የዘመናት የመልማት…
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል።…
የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ያውቀዋል ተላላኪው ግን ይጓጓል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን ዕድገት የማይፈልጉ ሀገራት በጦርነት ሊያሸንፉን እንደማይችሉ ያውቁታል። ነገር ግን የኢትዮጵያን አቅም ላኪው ቢያውቀውም ተላላኪው ግን ይጓጓል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ኢትዮጵያ ደካማ ሆና እንድትኖር ኢትዮጵያ በሁለት እግሯ መቆም እንዳትችል የሚሹና የሚሰሩ ሀገራት ባሉበት ሁኔታ ኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ለይተው…
Post Views: 135