Similar Posts
ወቅታዊ መረጃ
ሃገራችን ኢትዮጵያ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ የሚካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ከወትሮው በላቀ መልኩ በድምቀት ለማስተናገድ አስፈላጊውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ እንግዶቿን ለመቀበል ዝግጁ ሆናለች። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት ምስረታም ሆነ ከተመሰረተ በኋላ ከሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጋር በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጋለች። የኅብረቱ መቀመጫ እንደመሆናችንም በየዓመቱ የሚካሄዱ የአስፈጻሚዎች እና የመሪዎች ስብሰባዎችን በድምቀት ስናስተናግድ ቆይተናል። የአፍሪካ ኅብረት ሃገራችን ኢትዮጵያ ለፓን…
የፕሬስ መግለጫ
ኢትዮጵያዊነት ብያኔዉ የተሻለ ዓልሞ የላቀ ማሳካት ነው! ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ መነሻ፣ የጥቍር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲል ብቻ አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የመጪዉ ትውልድ የተስፋ ምድር ጭምር ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በጋራ ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር የሚገለጹ፣ የመቻል ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ “በጋራ እንችላለን” ብለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን እውን አደረጉ፡፡ “በጋራ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ” ብለው ላለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን…

ዓድዋ ድላችንም ቅርሳችንም ነው!
ዓድዋ ድላችንም ቅርሳችንም ነው! ኢትዮጵያ ጠንካራ ሥርዓተ መንግሥትና የጥንታዊ ሥልጣኔ ማዕከል ከነበሩ ሀገራት መካከል በግንባር ቀደምትነት ትጠቀሳለች፡፡ በዚህ ረዥም የታሪክ ጉዞ ኢትዮጵያ ሀገራችን ባሳለፈቻቸው የታሪክ ምዕራፎች ሁሉ ነፃነቷንና ሉዓላዊነቷን ለመጣስ ተከታታይ ወረራዎች ተፈጽመውባታል።ይሁን እንጂ የተቃጡባትን ወረራዎችና ጦርነቶች በአኩሪ ተጋድሎና መስዋዕትነት በመመከት የዓለማችን የነፃነት ቀንዲል ለመሆን በቅታለች። ሕዝቦቿ የሰውን ሀገር ግዛት ወርረው የማያውቁና የራሳቸውንም ስንዝር መሬት…

የዓድዋ ድል የዓላማ አንድነትና የጽናት ውጤት ነው!
ኢትዮጵያ በታሪኳ አንድም ጊዜ የሌላውን ፍለጋ ጥቃትና ወረራ ፈፅማ አታውቅም፡፡ በአንፃሩ ጠላቶችዋ በተለያዩ ዘመናት በተደጋጋሚ ከሩቅና ከቅርብ በኢትዮጵያ ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡ ሆኖም ግን ኢትዮጵያዊያን ተሸንፈው እጅ የሰጡበት ወቅት የለም፡፡ ሁሉንም ወራሪዎች ድል አድርገው አንገት በማስደፋት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር አስጠብቋል፡፡ከእነዚህ የወረራ ታሪክና የድል አድራጊነታችን የሁል ጊዜ ኩራታችን የሆነው ውቅያኖስን አቋርጠው ኢትዮጵያ ላይ ወረራ በመፈፀም ሉዓላዊነታችንን…

በሁከት እና ትርምስ ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረግ ሙከራ ጉም እንደመጨበጥ ነው- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
በሁከት እና ትርምስ ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማሳካት የሚደረግ ሙከራ ጉም እንደመጨበጥ ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ አስታወቀ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሰጠው ሳምንታዊ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ሀገራችን ኢትዮጵያ በለውጥ ሂደት ውስጥ ከገባች አምስት አመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የለውጥ ዓመታት ይሆናሉ ተብሎ ያልታሰቡ በርካታ ድሎች ተመዝግበዋል። በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካ ዘርፎች አገራችንን ወደፊት ሊያስፈነጥሩ የሚችሉ…