የማኅበረሰብ ሚዲያዉ ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስገንዘብ እና የወል ትርክትን ማስረጽ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባዉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስገነዘበ፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን በጉጉት ይጠብቃሉ፤ ጋራ ሸንተረሩም የዚህ አዲስ ዓመት ጠባቂ ይመስል ኩልል ባለ ንጹሕ የምንጭ ውኃ ፏፏቴ፣ በልዩ ልዩ ኅብረ ቀለማት አበቦች ይዋባሉ፡፡ አዲስ ዓመታችን ዐዳዲስ ዕቅዶችን መተግበር የምንጀምርበት፣ ተነፋፍቀዉ የከረሙ ተማሪዎችና መምህራን በጉጉት የሚገናኙበት፣ በመኸር የተዘራዉ የሚያሸትበት፣ ዐዲስ ተስፋና ጉጉት የሚፈነጥቅበት ነው፤ ለዚህም ነው በላቀ ጉጉት የሚጠበቀው፡፡የተጠናቀቀዉ 2016 ዓ.ም በፈተናዎች ውስጥ…
ማንኛዋም ሴት ከህልሟ እንዳትደርስ፤ ያሰበችውን ሰርታ እንዳታሳካ እንቅፋት የሚሆኑባትን ፆታዊ ጥቃቶች ማስቆም የሁላችንም ኃፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰራተኞችና አመራሮች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር በተመሰረተው ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች መቆያና መልሶ ማቋቋሚያ ማእከል ተገኝተው ድጋፍ በማድረግ በጋራ አክብረዋል። አገልግሎቱ የንፅህና መጠበቂያና…
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና የሚዲያ ሚና” በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሚዲያ ዋና አዘጋጆች፣ ምክትል ዋና አዘጋጆችና ከፍተኛ ባለሙዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ የአገልግሎቱ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አቶ ከበደ ዴሲሳ በሥልጠናዉ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ሥልጠናዉ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙዎች ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሞችና የመዳረሻ ትልሞች የወል መረዳት እንዲኖራቸዉ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡“የሀገራዊ ገዥ ትርክት ግንባታ ምንነትና…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል። የባህር ዛፍን በሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የመተካቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ ተካፋይ እንዲሆን ጠቅላይ…
በግብርና ዘርፍ ያገኘናቸው ስኬቶች በኢንዱስትሪው ዘርፍም በመደገም ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር በቀል አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አሳድጓል ንቅናቄው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት፣ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በጥራትና በብዛት ለማምረት እንዲሁም የግብርና እና ማዕድን ምርቶች ላይ ዕሴት ጨምሮ ለገበያ ለማቅረብ አዲስ ምዕራፍም ከፍቷል።በተለይ በጎጆ ኢንዱስትሪ የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴ አካል የሆነው የገቢ ምርቶችን…
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017(የኢፌዴሪ መ.ኮ.አ) “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት “በሚል መሪ ቃል 19ኛው የብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ተከብሯል ። በመርሐ ግብሩ የአገልግሎቱ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ለገሠ ቱሉን ጨምሮ ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ እና የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዝናቡ ቱኑ ተገኝተዋል ። በዓሉ በተለያዩ ሁነቶች የተከበረ ሲሆን…