የሪፎርም ስኬትና የማይበገር ኢኮኖሚ ግንባታ

መንግሥት ሀገር በቀል ሪፎርሞችን በመተግበር፣ ኢኮኖሚውን ለውድድር ክፍት በማድረግ እና ስር የሰደዱ መዋቅራዊና ኢኮኖሚያዊ ማነቆዎችን በስኬት በመሻገር ተጨባጭ ለውጦች እንዲመዘገቡ አድርጓል ። ባለፉት ዘጠኝ ወራት የታየው የ9.2 በመቶ ዕድገት በቀጣይ ወደ 10.2 በመቶ ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል። የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከ8 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ወጥተው 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ አስገኝተዋል። በ2,153 የኢንቨስትመንት ፈቃዶችና በማምረቻ ዘርፉ የ46 በመቶ የገበያ ድርሻ ዕድገት ከ96,000 በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል። እነዚህ ስኬቶች ከብሪክስ (BRICS) አባልነትና ከኮፕ 32 (COP32) ዝግጅት ጋር ተዳምረው መንግሥት በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በአረንጓዴ ልማትና በጠንካራ ዲፕሎማሲ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳዩ ናቸው ።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts