የተሻገረ ምርትን ለማምጣት ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ሚና አለዉ!

ሚያዚያ 6/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዙሪያ በሰጡት ቃለ-ምልልስ፤ ዘርፉ የኢኮኖሚው ልብ እና የሀገር ሉዓላዊነት መሠረት መሆኑን በዝርዝር አብራርተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ ኢንዱስትሪው ምርታማነትንና የኤክስፖርት መጠንን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን የማነቃቃት ልዩ አቅም አለው። በተለይም የጥሬ ዕቃ አቅራቢነትን ደረጃ በመለወጥ፣ እሴት በመጨመርና ምርቶችን በብዛትና በጥራት የማምረት አቅምን በማጎልበት ረገድ ዘርፉ ለኢኮኖሚው መዋቅራዊ ሽግግር አይተኬ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

አክለውም፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራን ወደ ሌሎች ዘርፎች በተለይም ወደ ግብርናው በማስገባት ረገድ ኢንዱስትሪው ያመጣውን ተጨባጭ ለውጥ እንደ አብነት ጠቅሰዋል። በመጨረሻም፣ ዘርፉ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ያለውን ከፍተኛ ድርሻ በመጠቆም፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሚገኘው ውጤት ለኢኮኖሚ ዕድገቱ መፋፋም ዋነኛ ምክንያት መሆኑንና ማኑፋክቸሪንግ የሀገር ሉዓላዊነት ዋነኛ አጀንዳ መሆኑን አመላክተዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts