የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (COP)፤ በየዓመቱ የሚካሄድ የዓለማችን ትልቁ የአየር ንብረት መድረክ ነው።

‎ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2027 የሚካሄደውን 32ኛውን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ COP32 እንድታስተናግድ መመረጧ፤ የሀገሪቱን ዓለም አቀፋዊ ተሰሚነት ለማሳደግ፣ በመሰረተ ልማት እና በአረንጓዴ ልማት ዘርፎች ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል። ዓለም አቀፍ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ድርጅቶች የሚታደሙበት ይህ ታላቅ ሁነት፤ የኢኮኖሚ እድገትን ያነቃቃል፣ የሥራ ዕድል ይፈጥራል እንዲሁም የሀገር ውስጥ ንግድን ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም በሕዝብ አገልግሎቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ዐቅም ላይ የሚታየውን ዕድገት ያፋጥናል። በአጠቃላይ ይህ ጉባዔ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዘላቂ ልማት እንድታጠናክር የሚያስችላት ሲሆን፤ ለዜጎቿም ትርጉም ያለውና ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ ነው።

#PMOEthiopia

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ለዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ ሁነት፤ እያደረገ ያለው ዝግጅት እና እርስዎም እንደ አንድ ዜጋ ለጉባዔው ስኬት ምን ዓይነት ሚና መጫወት እንደሚችሉ ጠልቀው ይረዱ!

Similar Posts