የአገው ፈረሰኞች ከሌሎች ኢትዮጵያን ጋር ተባብረው የኢትዮጵያን ነጻነት እንዳስከበሩት ሁሉ እኛም የዚህ ዘመን ትውልዶች የአባቶቻችን መስዋዕትነት በማስታወስ የሚጠበቀውን የብሔራዊነት ግዳጅ ልንወጣ ይገባል!

አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል “አርበኝነታችን ለአሁናዊ ሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት በእንጅባራ ከተማ በድምቀት እየተከበረ የሚገኘው በዓል ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ፤
የአገው ፈረሰኞች ከሌሎች ኢትዮጵያን ጋር ተባብረው የኢትዮጵያን ነጻነት እንዳስከበሩት ሁሉ እኛም የዚህ ዘመን ትውልዶች የአባቶቻችን መስዋዕትነት በማስታወስ የሚጠበቀውን የብሔራዊነት ግዳጅ ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
ጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያን ቀኝ ለመግዛት የመጣውን ቅኝ ገዢ አሳፍረው በመመለስ የመንፈስ ብርታት አውርሰውናል ብለዋል።
ለሀገር መስዋዕትነት የከፈሉ ፈረሶችን እና ፈረሰኞችን ለመዘከር የአገው ፈረሰኞች በዓል በየዓመቱ እንደሚዘከር ያመላከቱት ሚኒስትር ዴኤታው ፈረስ ከአገው ሕዝብ ጋር የጠበቀ ግንኝነት እንዳለው እና የአገው ሕዝብ የሀገሩን አንድነት እና ማኅበራዊ ማንነቱን በሁለንተናዊ ጀግንነት አጽንቶ የኖረ ሕዝብ መኾኑንም ገልጸዋል።
የአገው ፈረሰኞች በዓል የአገው ሕዝብ ለሀገሩ ክብር ዋጋ የከፈሉትን ሁሉ አክብሮ የሚያስከብር አስተዋሽ ሕዝብ መኾኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የአገው ፈረሰኞች ከሌሎች ኢትዮጵያን ጋር ተባብረው የኢትዮጵያን ነጻነት እንዳስከበሩት ሁሉ እኛም የዚህ ዘመን ትውልዶች የአባቶቻችን መስዋዕትነት በማስታወስ የሚጠበቀውን የብሔራዊነት ግዳጅ ልንወጣ ይገባል ሲሉ በአጽኖት ተናግረዋል።
በዓሉን በድምቀት ማክበር የቻልነው ሰላም በመስፈኑ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የተሟላ ሰላም በአማራ ክልል እና በመላው ሀገራችን እንዲሰፍን መንግሥት ስላማዊ አማራጭን ከሚከተሉ ጋር ሰላማዊ አማራጭን ለመጠቀም በሩ ክፍት መኾኑን ነው የተናገሩት።
የሰላም አማራጭን ለሚመርጡ ወንድም እህቶቻችን በድጋሜ ጥሪ እናስተላልፋለን ብለዋል ።
ኢትዮጵያ የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ፣ ታሪካዊ እና ባሕላዊ ኹነቶችን በዩኔስኮ ማስመዝገቧን እና አሁን በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ እየተሠሩ ካሉ ኹነቶች መካከል አንደኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል መሆኑን ገልጸዋል።