የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ
የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መዋቅራዊ ማነቆዎችን በመፍታትና የአምራች ዘርፉን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ሀገራዊ ብልጽግናን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተደረገ የተቀናጀ ጥረት፣ በዘርፉ የታየው ዕድገትና የተመዘገቡት ስኬቶች የኢንዱስትሪውን መፃኢ ዕድል ብሩህ አድርገውታል።
ዋና ዋና የሥራ አፈጻጸም ስኬቶች፦
የአምራችነት አቅም ሽግግር
• አማካይ የማምረት አቅም ከ47% ወደ 67% ከፍ ብሏል።
• የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገት ከ4.8% ወደ 10.7% በማደግ የምርት መጠንን 195.4 ቢሊዮን ብር አድርሷል።
• የማኑፋክቸሪንግ እሴት ጭማሪ ወደ 8.4% አድጓል።
የኢንቨስትመንትና የሥራ ዕድል ፈጠራ
• ወደ ምርት የሚገቡ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር ከ26 ወደ 131 አድጓል።
• ባለፉት 8 ዓመታት ለ 1.4 ሚሊዮን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን፣ በየዓመቱ በአማካይ 280 ሺህ አዳዲስ የሥራ ዕድሎች ወደ ኢኮኖሚው እየገቡ ይገኛሉ።
የፋይናንስና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት
• ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የቀረበው ብድር ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር አድጓል።
• ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የቀረበው ብድር ከ52 ቢሊዮን ወደ 262 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
• ለከፍተኛ አምራቾች ከ 2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ የቀረበ ሲሆን፣ በየዓመቱ የ14% አማካይ ዕድገት እያሳየ ይገኛል።
የምርት ጥራትን በማሳደግና ተኪ ምርቶችን በስፋት በማምረት፣ ኢትዮጵያን የአምራችነት ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት እንቀጥላለን!
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers #MadeInEthiopia
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

