የኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት፣ የመቋቋም አቅም እና የሀገር ልማት ስትራቴጂን መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ደህንነቱ የተጠበቀ የዲጂታል ፈጣን የሽግግር ለውጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት ይገኛል፡፡
በተለይ በሳይበር ጥቃቶች ላይ የመቋቋም አቅምን፣ የአቅም ግንባታን፣ ጠንካራ የህግ ማዕቀፎችን እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትኩረት ተደርጓል፡፡ ስትራቴጂው ከአገር አቀፍ የልማት ግቦች ጋር የሚጣጣም፣ በሳይበር መረብ ላይ እምነትን ከማሳደጉም ባሻገር ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና የደህንነት ፍላጎቶችን መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡
በተጨማሪም ከሀገሪቱ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ራዕይ ጋር የሚስማማ ሲሆን ይህም ቴክኖሎጂን ለአካታች የኢኮኖሚ እድገት፣ ለተሻሻለ የህዝብ አገልግሎት እና ለፈጣን የህዝብ አስተዳደር ለማዋል ያለመ ነዉ፡፡
መንግስት ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ ብሎም ደህንነታቸው የተጠበቀ የዲጂታል መረጃ ልዉዉጦች እና የፋይናንስና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ላይ የህዝብ እምነትን ለመገንባት ጠንካራ የሳይበር ደህንነት እርምጃዎች አስፈላጊ መሆናቸውን አፅንዖት በመስጠት እየሰራበት ይገኛል፡፡
በሀገሪቱ የዲጂታል አገልግሎቶች ከፋይናንስ፣ ከጤና አገልግሎት፣ ከትምህርት እና ከግብርና ልማት ዘርፎች በጣም እየተስፋፋ በመሆኑ የመቋቋም አቅም ያላቸው የሳይበር ጥቃት መከላከያዎችን ማጠናከር ወቅቱ የሚጠብቀዉ ጉዳይ ሆኗል፡፡
የመንግስት የፖሊሲ አቅጣጫው የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ በሳይበር ደህንነት ላይ ኢንቨስት ማድረግ እና የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የመንግስት ተቋማትና የግል ድርጅቶችን ማጠናከር ትኩርት አድርጓል፡፡

