የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል
የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አካባቢን በመጠበቅ ለዘላቂ እድገት የሚሆን ግብዓት በመሆን እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት በማስፋት ሀገራዊ ግቦችን በማሳካት ትልም ላይ የተቃኘ ነው።
ሀገራችን እንደ የውሃ ኃይል፣ የንፋስ፣ የፀሐይ እና ጂኦተርማል ያሉ ንፁህ የኃይል ምንጮችን ቅድሚያ በመስጠት በከሰል እና ነዳጅ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ እየሰራች ትገኛለች።
እነዚህ ጥረቶች ለዜጎች እና ኢንደስትሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብና የሀገር ውስጥ ምርት እንዲጠናከር በማስቻል የሥራ ዕድል ፈጠራን ይደግፋል።
የኃይል አቅርቦት አገልግሎት ላልደረሳቸው ዜጎች አገልግሎቱን ያዳርሳል። በድምሩ የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ሥራዎች ለጽኑ እና ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ የኢኮኖሚ ምኅዳር በማመቻቸት የረጅም ዘመን የኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ያጎናፅፋሉ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
