የእንጦጦ – ቀበና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት በጥቂቱ፦
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ከያዛቸው መሰረተ ልማቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፤
- የወንዝ ልማት፦ 1 ትልቅ ግድብ፣ 16 አነስተኛ ግድቦች፣ 3 ቼክ ዳሞች እና 20.2 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ።
- የወንዝ ዳርቻ ልማት፦ 36,928 ካ.ሜ የአፈር እና ስነ-ምህዳር ጥበቃ ስራዎች (የኮንሶ ጋቢዮን እና እርከን)።
- አረንጓዴ ልማት፦ 59.7 ሄክታር የአረንጓዴ ሽፋን እና 50,330 የተተከሉ ዛፎች።
- የተቀናጀ መሰረተ ልማት፦ 21 የእግረኛ ድልድዮች፣ 33.2 ኪ.ሜ የውስጥ መንገዶች፣ የፍሳሽ መስመር እና 695 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችሉ 7 ቦታዎች።
ይህ ፕሮጀክት ስነ-ምህዳሩን ከመቀየር ባለፈ፣ በውስጡ በያዛቸው ሱቆች፣ ካፌዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎች አዳዲስ የንግድና የኢኮኖሚ እድሎችን በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል።











