የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሶስቱ ግቦች

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ መንደርደሪያ ያደረገዉ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025”ን ሲሆን በዋናነት ሦስት ግቦችን ለማሳካት ዓላማ ያደረገ ነዉ፡፡

አንደኛዉ ግብ ተደራሽነትን ማስፋት ሲሆን ይህም ሁሉም ዜጎች ከቤታቸዉ፣ ከስልኮቻቸዉ እና ካሉበት ስፍራ ሆኖ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠር ነዉ፡፡

ሁለተኛዉ ግብ ለዜጎች እኩል እድል መስጠት ነው፡፡ መንግሥት እኩል እድል ባልሰጠበት ሁኔታ የዜጎች እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ስለማይቻል ሁሉም ዜጎች ሊያገኙ የሚገባዉን እኩል እድልና የአገልግሎት ሥርዓት ማመቻቸትን መሰረት ያደረገ ነዉ፡፡

ሶስተኛዉና ዋንኛዉ ግብ ደግሞ መተማመንን መፍጠር ሲሆን፣ በዜጎች እና በተቋማት መካከል የመተማመን ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል ነዉ፡፡ በተቋማትና በዜጎች መካከል መተማመን ካልተፈጠረ በሁሉም መስኮች ማለትም በመማር ማስተማር፣ በገንዘብ ልዉዉጥ፣ የጤና መረጃ መለዋወጥና የመሳሰሉ ስራዎችን መሥራት የሚታሰብ አይሆንም፡፡

ስለዚህ ዜጎች ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱና እምነት እንዲኖራቸዉ ማድረግ በሁሉ ነገር ትምምን እንዲፈጠርና ለዉጤታማት የሚያበቃ ነዉ፡፡

በአጠቃላይ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ሶስቱ ግቦች ተደምረዉ ለዜጎች በርከት ያለ የስራ እድል መፍጠር፣ የሀገር እድገትንና ሉዓላዊነትንም ጭምር ማረጋገጥ አለባቸዉ፡፡ ይህንን ራዕይ በትብብርና በጋራ እንደሚናሳካም ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ተጨማሪ መረጃ

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts