የገጠር ትሥሥር
መንግሥት የሐገሪቱን አርሶ አደሮችን ከአካባቢያቸው እና ከክልል የገበያ ስርዓቶች ጋር ለማስተሳሰር የገጠር መንገዶችን እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማስፋፋት ላይ ይገኛል። ይህም በመላ ሀገሪቱ የሸቀጦች እና የግብዓቶች ዝውውር እንዲሻሻል እያደረገ ነው። እነዚህ ተግባራቶች ይወስድ የነበረውን የጉዞ ስዓት እና የትራንስፖርት ወጪን በመቀነስ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በብቃት እንዲሸጡ፣ ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም እንደ ጤና ጥበቃ፣ ትምህርት እና የግብርና ድጋፍ ያሉ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል። በጥቅሉ የተሻሻለ የትስስር መረብ የአካባቢ ኢኮኖሚን ከማጠናከሩ ባለፈ፤ ልማት በሁሉም የሐገሪቱ ክፍሎች እንዲዳረስ በማድረግ አካታች እድገት እንዲሰፍን አይተኬ ሚና ይጫወታል።
