የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂጃለሁ። ውይይታችን በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ነበር። በተጨማሪም፣ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳየውን የመደመር መጽሐፌን የሩሲያኛ ዕትም ለፕሬዚዳንት ፑቲን አበርክቼላቸዋለሁ።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts