የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“በአምስት ዓመታት ውስጥ ቤቶችን ገንብተን ለማስረከብ ለሕዝባችን ቃል ገብተናል፤ ይህንንም ቃላችንን በተግባር ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ያለ እረፍት እየተጋን እንገኛለን። ሕዝባችን በመኖሪያ ቤት እጥረት ምክንያት የሚገጥመውን ፈተናና ስጋት በሚገባ እንረዳለን፤ ደረጃቸውን የጠበቁና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶችን ማመቻቸት የልማት ግብ ብቻ ሳይሆን፣ ለዜጎቻችን ያለብን አደራና ኃላፊነት መሆኑንም ጠንቅቀን እንገነዘባለን።
ዋነኛ ትኩረታችን ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ፣ የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ማቃለል እና በመላው አገሪቱ ለሚገኙ ቤተሰቦች የተሻለ የኑሮ ምዕራፍ መክፈት ነው።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication








