የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ውድ ኢትዮጵያዊያን
በዚህ ሳምንት ውዷ ሀገራችን በአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ለመታደም የሚመጡ እህት ወንድም አፍሪካዊያንን ለመቀበል ልቧን ከፍታ-እጆቿን ዘርግታ ትቀበላለች። እነዚህ ወዳጆቻችን የሰንደቃችንን ቀለማት የሚጋሩ፣ ኢትዮጵያን እንደነፃነት ቀንዲል የሚመለከቱ ብሎም ሀገራችን የአኅጉሩ የፖለቲካ ርዕይ የማዕዘን ድንጋይ አድርገው የሚያከብሩ ናቸው።
ኢትዮጵያ ወደር በሌለው እንግዳ ተቀባይነቱ ለምን ልትከበር እንደበቃች በአቀባበላችን እናሳያቸው። እንደቤታቸው እንዲሰማቸው እናድርግ። በክብር እንቀበላቸው። በፍቅር እናቆያቸው። ተደምረን ሰንደቃችን የሚወክለውን የአፍሪካ አንድነትን መንፈስ እና የሚያያይዘንን የወል ህልም እናድርግ!
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

