የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ዛሬ ወደ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ጉብኝት አድርገናል። ጉብኝቱ የሀገራችንን ብሔራዊ የሎጂስቲክስ ክዋኔ ዐቅም ለመገምገም እና የሀገሪቱን እያደገ ያለ የልማት አጀንዳ ለመደገፍ በሎጂስቲክስ ዝግጁነት ላይ ገንቢ ውይይቶችን ለማካሄድ ጠቃሚ ዕድል ሰጥቶናል።
ኢኮኖሚያችን እያደገ ሲሄድ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ካልዘመነ ዘላቂ ዕድገትን የሚገድብ ዋና መሰናክል መሆኑን ይቀጥላል። አሁን በተለይ በውስጣዊ እና በራስ ዐቅም የባቡር መንገድ ግንባታ ላይ የተመዘገበው ዕድገት እጅግ የሚያስደንቅ ነው። ይህም የሀገር ውስጥ ዐቅምን ለመገንባት፣ ውጤታማነትን ለማሻሻል እና በባቡር ዘርፍ ውስጥ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት ያሳያል።
ሎጂስቲክስ ከባሕር እስከ መጋዘኖች ድረስ ያለውን ሙሉ ሰንሰለት ያካትታል። ይህም ወደቦች፣ የባቡር መንገዶች፣ አውራ ጎዳናዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች እና የማከማቻ ተቋማትን ይጨምራል። በአሁኑ ወቅትም በእጃችን ውስጥ ባሉ መስኮች ላይ እንደ ደረቅ ወደቦች፣ የባቡር መሠረተ ልማት፣ አውራ ጎዳናዎች እና የመጋዘን ግንባታ አስፈላጊ ማሻሻያዎችና ዘመናዊ የማድርግ ሥራዎች በሂደት ላይ ናቸው። እነዚህን ተያያዥ የሎጂስቲክስ ክፍተቶችን በተቀናጀ መንገድ መፍታት የዘርፉን መሰናክሎች ለመሻር እና የሀገሪቱን ሰፊ የልማት ግቦች ለመደገፍ ወሳኝ ይሆናል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication






